Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከሃይፈር ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንት ሱሪታ ሳንዶሻ ጋር ተወያዩ፡፡

June 27, 2023
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በዓለም አቀፍ ደረጃ ድህነትን እና ረሃብን በዘላቂነት ለመቀነስ ከሚሰራው የሃይፈር ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንት ሱሪታ ሳንዶሻ ጋር በነበራቸው ቆይታ ሁለንተናዊ የማህበረሰብ ልማት ከማፋጠን አንፃር የእሴት ሰንሰለትን መሰረት ያደረገ ሥልጠና መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል፡፡ በቀጣይም በክህሎት ልማቱ ዘርፍ ወጥነት ያለው የትብብርና የቅንጅት ሥራን ከድርጅቱ ጋር ለመስራት ተግባብተዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top