Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ቪዥነሪ የምዘናና ሥልጠና ማዕከልን ጎበኙ

December 5, 2024
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ቪዥነሪ የምዘናና ሥልጠና ማዕከልን ጎበኙ የክህሎት ልማት ሥራችን በሥራ ገበያው ፍላጎት ጀምሮ በሙያ ብቃት ምዘና የሚጠቃለል ነው፡፡ በመሆኑም ከክህሎት ስልጠናው ባልተናነሰ መልኩ ወደ ሥራ ገበያው የሚቀላቀለው የሰው ሃይል ብቃቱ የተረጋገጠ እንዲሆን የምዘና ስርዓቱ ወቅቱን በዋጀ ቴክኖሎጂ የሚደገፍ እና ቀጣሪ ድርጅቶችም ለሚሰጠው የምዘና ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ዋጋ እንዲሰጡት በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ዓለም አቀፍ የሥራ ገበያውን ለመጠቀም በምናደርገው ጥረት ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው ተቋማት የሚሰጡት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ወሳኝ በመሆኑ እነዚህ ተቋማት ለዜጎቻችን ተደራሽ የሚሆኑበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በዚህም ቪዥነሪ የምዘናና ሥልጠና ማዕከል ዓለም አቀፍ እውቅና ካላቸው የምዘና ተቋማት ጋር በመተባበር የከፈተውን የምዘና ማዕከል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ጎብኝተዋል፡፡ ከማዕከሉ የሥራ አመራሮች ጋር በምዘና፣ ስልጠናና እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያም ውይይት አካሂደዋል፡፡ በውይይቱ ማዕከሉ በዚህ መልኩ ሥራ መጀመሩ በውጭ ሀገር ያሉ የሥራ ዕድሎችን ከማስፋት ባሻገር በትምህርትና ሥልጠናው መስክ ሙያዊ እድገትንና የዕድሜ ልክ ትምህርትን የሚያበረታታ እንዲሁም እንደ ሀገር ያለንን ተወዳዳሪነትን የሚጨምር እንደሆነ ተመላክቷል፡፡ በመስኩ የግሉ ዘርፍ ሚናም ከፍተኛ እንደሆነ ተጠቁሟል::
en_USEN
Scroll to Top