Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የተገነቡ ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ቤት እና የመማሪያ ክፍሎች ቁልፍ ለተጠቃሚዎች አስረከቡ።

July 26, 2025
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የተገነቡ ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ቤት እና የመማሪያ ክፍሎች ቁልፍ ለተጠቃሚዎች አስረከቡ። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመሆን በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ባቢሌ ከተማ ከ25 ሚለየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባቸው ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ቤት እና የትምህርት ቤት ማስፋፈፊያ ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል ለተጠቃሚዎች አስረክበዋል። በመርሃ ግብሩ የተገኙት ክብርት ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣የሚኒስቴሩ እና የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች እና የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ ምስኪ መሀመድን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አረንጓዴ አሻራቸውንም አኑረዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በርክክብ መርሃ ግብር ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት ባለፉት ዓመታት ሰው ተኮር የሆኑና የዘመሙ ጎጆዎችን የሚያቀኑ እጅግ በርካታ ስኬታማ ስራዎች ማከናወኑን ገልጸው ከነዚህ መካከል የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል። ሚኒስቴሩም የዜጎችን ህይወት ለማሻሻል በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው እነዚህ ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ቤት እና የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ የዚሁ ሥራ አካል መሆኑን ገልጸዋል። ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ቤት የተገነቡ 10 መኖሪያ ቤቶች እና በባቢሌ አንደኛ ደረጃ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 ትምህርት ቤቶች የተገነቡ 8 የመማሪያ ክፍሎች ወጪ ቆጣቢ በሆነ ቴክኖሎጂ የተከናወኑ መሆኑን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር ይህም ለቴክኖሎጂ ሽግግር ያለው ፋይዳ የጎላ ነው ብለዋል።
en_USEN
Scroll to Top