Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

May 10, 2024
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ጋር ውይይት አካሂደዋል። ውይይቱ ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያ ሁለቱ ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ ያለመ ነው። በዚህም በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ላይ የተደረገውን ሪፎርም ተከትሎ በዘረጋው የጋራ የአሰራር ስርዓት የተከናወኑ ሥራዎችን፣ ያጋጠሙ ችግሮችን እና ችግሮቹን ለመሻገር የሚወሰዱ እርምጃዎችን በዝርዝር ተመልክተዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ግልጽና የተቀላጠፈ አሰራር ስርዓትን በማስፈን የተጀመሩትን በቴክኖሎጂ የታገዙ ሥራዎችን ማላቅ በሚያስችል መልኩ የሚዘጋጅበት ሁኔታ ላይም መክረዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top