Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር 20ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር አከበረ

November 24, 2023
”ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፣ በህብረት እንታገል” በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተከበረ የሚገኘው የዓለም የጸረ ሙስና ቀን የፌደራል የፀረ ሙስና ኮሚሽን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ በጋራ አክብረዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አሰግድ ጌታቸው በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፤ ሙስና እና ብልሹ አሰራር ጥቂቶችን በጊዚያዊነት የሚጠቅም ብዙሃኑንና ሀገርን በዘለቂነት የሚጎዳ ጸያፍ ተግባር በመሆኑ የተባበረ የፀረ-ሙስና ትግል ማድረግን ይጠይቃል ብለዋል፡፡ ሙስና የሰው ልጆችን የማስተዋልና የጥበብ ምንጭ የሚያደርቅ ጣፋጭ መርዝ ነው ያሉት ክቡር ዶ/ር አሰግድ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማቱ አመራርና ሠራተኞች ጉዳቱን የሚመጥን ትግል ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡ የፌዴራል የፀረ-ሙስና ከሚሽን ም/ል ኮሚሽነር አቶ እሸቴ አስፋው በበኩላችን፤ የዘንድሮ የሙስና ቀን ስናከብር በተልዕኮ እና በተግባር እንዲሆን በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት አመራሩ ሀብቱ እንዲያስመዘግብ ከማድረግ ጀምሮ ተጨባጭ ሥራዎች እየተሰሩ እየተከበረ ነው፡፡ ሙስና ለሀገር ስጋት መሆን ስለታመነበት በሀገር አቀፍ ደረጃ የፀረ ሙስና ትግል ግብረ-ሀይል በማቋቋም የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡ በመድረኩ የሙስና መከላከል እና የአመራሩ ሚና በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡
en_USEN
Scroll to Top