Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች …

April 8, 2024
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ተግባራዊነትን ለመከታተልና ለመደገፍ ባለመውና በከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሚመራው ቡድን በክልሎችና በከተማ አስተዳድሮች እያደረገ ያለው የመስክ ምልከታ እንደቀጠለ ነው፡፡ የመስክ ምልከታው ዓላማ መልካም አፈፃፀሞችን ማስፋት፣ ማነቆዎችን መፍታት እና ድጋፍ የሚፈልጉ ሥራዎችን ለይቶ በመደገፍ በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና በሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ላይ የተቀመጡ ግቦች እንዲሳኩ መደላድል መፍጠር ነው፡፡ በዚህም የተመረጡ ዘጠኝ ክልሎችና ሁለቱም ከተማ መስተዳድሮች ላይ ቢሮዎች፣ አንድ ማዕከላትና ማሰልጠኛ ተቋማት ጨምሮ በሪፎርሙ እሳቤ መሰረት በተጨባጭ የተፈጠሩ የሥራ ዕድሎች፣ እየተሰጡ ያሉ ሥልጠናዎችን እና የኢንዱስትሪ ሰላም ጋር ተያይዞ የተከናወኑ ሥራዎች እየታዩ ይገኛል፡፡
en_USEN
Scroll to Top