Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር..

December 13, 2023
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በስትራቴጂካዊ አጋርነት ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂና በኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት እንዲሁም ተያያዥ በሆኑ ተግባራት ላይ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በስትራቴጂካዊ አጋርነት ለመሥራት የሚያስችለውን የፊርማ ሥነ-ሥርዓት አካሄዷል፡፡ በፊርማው ሥነ- ሥርዓት ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የተለያዩ መስኮች ላይ በጋራ ሲሰራ መቆየቱን በማስታወስ ይህን አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር እንዲቻል የጋራ ሥምምነቱ መፈረሙን አስታውቀዋል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም ከሥራ ዕድል ፈጠራ አኳያ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ጉልህ ሚና መጫወት እንደሚችል የጠቀሱት ክብርት ሚኒስትር በቀጣይም ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድልን ለመፍጠር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ማመቻቸት የሥምምነቱ አንድ አካል መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የሚተገበረውን የ e- learning ስርዓት ማጠናከር፣ ኢትዮ ቴሌኮም ተግባራዊ ከሚያደርገው የፋይናንስ ስርዓት ኢንተርፕራይዞች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሥርዓት መዘርጋትና የ e-commerce ሥርዓትን በመጠቀም ኢንተርፕራዞች ምርትና አገልግሎታቸውን ለገበያ እንዲያቀርቡበትን ዕድል ማመቻቸት በሥምምነቱ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች መሆናቸውን ክብርት ሚኒስትር አስረድተዋል፡፡ ወደ ውጭ አገር ህጋዊ በሆነ መንገድ ለሥራ የሚሄዱ ዜጎች የስልክ ቁጥራቸውን በመዳረሻ አገራትም መጠቀም የሚችሉበትን ሥርዓት ማመቻቸትም የሥምምነቱ አንድ አካል መሆኑ ተገልጿል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ በበኩላቸው ኢትዮ ቴሌኮም ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በሥትራቴጂካዊ አጋርነት አብሮ ለመሥራት የደረሰበት ሥምምነት የቴክኖሎጂና የፋይናንስ አገልግሎትን በፍትሃዊነት ተደራሽ ከማድረግና የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንፃር ጉልህ ሚና እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top