Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የጋራ ዕቅድ ትግበራ ሥምምነት ተፈራረሙ፡፡

November 22, 2022
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የጋራ ዕቅድ ትግበራ ሥምምነት ተፈራረሙ፡፡ ስምምነቱን የፈረሙት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር አቶ ገ/መስቀል ጫላ ናቸው ፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ስምምነቱ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የጥራት መሰረታዊ ደረጃዎችን የሚያወጣና የሚመራ እንደመሆኑ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚከናወኑ ስራዎች ጥራትንና ተወዳዳሪነት ማዕከል ያደረጉ ትልቅ አብክቶ ይኖረዋል ብለዋል፡፡ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር የንግድ ስርዓቱ የሚያዘምኑ ግቦችን ለመተግበር፣ በክህሎት ልማት እና የሥራ ዕድል ፈጣሪነት አስተሳሰብ ላይ በጋራ የሚሰሩ በርካታ ስራዎች መኖራቸዉን ገልጸዉ ለጋራ እቅዱ ተግባራዊነቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስትር ክቡር አቶ ገ/መስቀል ጫላ በበኩላቸዉ ስምምነቱ ለንግዱ ማህበረሰብ ተወዳዳሪነትና ቅልጥፍና ወሳኝ የሆነውን የሰዉ ሃይል ምርታማነት ከማጎልበት አንፃር ቁልፍ ሚና አለዉ ብለዋል፡፡ በተለይም ወደ ንግድ ሥርዓቱ ለሚገቡ አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠርና እና ስራ አጥነት ለመቀነስ ይህ የጋራ እቅድ ትልቅ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል፡፡
Scroll to Top

The Ministry of Labor & Skills