Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ ለሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ከአርባ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡

November 22, 2022
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ ለሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ከአርባ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻን ጨምሮ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እንየው ጌትነትና የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በመከላከያ ሚኒስቴር ተገኝተው ድጋፉን ለክብርት ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ሉጂ አስረክበዋል፡፡ እስከ አሁን የተደረገው ድጋፍ ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ በገንዘብና ቀሪው በአይነት የተበረከተ ነው፡፡
en_USEN
Scroll to Top