የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራሮች በፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ከተቋቋመውና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱንና እና የተጠሪ ተቋማትን የበጀት ዓመቱን ዕቅድ የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ከሚገመግመው የሱፐርቪዥን ቡድን ጋር የመግቢያ ውይይት አካሂደዋል፡፡
በክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የሚመራው ይህ የሱፐርቪዥን ቡድን በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በተከናወኑ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮች፣ በሥራ ገበያ አስተዳደር ስርዓትና በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገልግሎት ላይ በማተኮር ምልከታውን ያካሄዳል፡፡
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን አፈጻጸም መነሻ በማድረግ ከፖሊሲ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ላይ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን መለየት የሱፐርቪዥን ምልከታው ከሚያተኩርባቸው ጉዳዮች መካከል ዋንኛው መሆኑ ተገልጿል፡፡
ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታትና ማነቆዎችን ለመፍታት መወሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች ማመላከትም ከቡድኑ የሚጠበቅ ሌላው ውጤት መሆኑም በመድረኩ ተብራርቷል፡፡