Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች የ2016 በጀት ዓመት …

March 14, 2024
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች የ2016 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ሀገራዊ የዘርፎች ዕቅድ አፈጸጸም ላይ ውይይት አካሄዱ። በመድረኩ ሀገራዊ የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል። ውይይቱ ሀገራዊ ዕቅድና አፈፃፀምን አውቀን በሂደቱ የበኩላችንን ሚና መወጣት እንድንችል ዕድል የሚሰጥ ነው ሲሉ ተሳታፊዎች አንስተዋል። የሥራ አጥነትን ምጣኔ ትርጉም ባለው መልኩ መቀነስ፣ ምርትና ምርታማነትን ማሻሻል የሚያስችል የሰው ሀይልና የቴክኖሎጂ ልማት፣ ቅንጅታዊ አሰራርን ማላቅ፣ የሀገር ውስጥ ምርትን ለማበረታታት ምርቶቹን መጠቀምና ተኪ ምርቶችን ማሳደግ፣ ሙስናን መቀነስ እና ስታርትአፓችን ማበረታታት የሚያስች ስነ ምህዳር ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ ማስቀጠል በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸው ተጠቁሟል።
en_USEN
Scroll to Top