Mols.gov.et

“የምርታማነት ውይይት” በሥራ ባህል እና…

December 27, 2023
“የምርታማነት ውይይት” በሥራ ባህል እና ምርትና ምርታማነታችን ላይ ተጨባጭ ለውጥ ሊያመጣ የሚያስችል መሆኑ ተገለፀ ይህ የተገለፀው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በዘርፉ የሪፎርም እሳቤዎች እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ በየደረጃው ካሉ አመራሮች ጋር እያካሄደ በሚገኘው የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የምክክር መድረክ ላይ ነው፡፡ በመድረኩ ኢትዮጰያ ተዝቆ የማያልቅ የመልማት ፀጋ ያላት ሀገር መሆኗ እና እስካሁን ይህን ሀብት በአግባቡ አልምቶ ለመጠቀም ላለመቻሉ መንስኤዎቹ ተነስተዋል፡፡ ይህንን ነባራዊ ተቃርኖ ለመፍታት ዘርፉ የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ መከተል ስለሚገባው አቅጣጫዎችና የርብር ማዕከላትም ተመላክተዋል፡፡ በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ባስተላለፉት መልዕክት፤ እንደ ዘርፍ በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ላይ የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ የሪፎርም ሥራዎች መሰረትረታቸውና አድማሳቸውን ለማስፋት በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሆ ገልፀዋል፡፡ በዚህም ዘርፋችን አስቻይ ሚና ያለውና የሥራ ባህልና ምርታማነትን ከማሳደግ አኳያ የባህሪ ለውጥ የሚያመጡ ሥራዎችን መተግበር እንደሚያስፈልግ እና ለዚህም ህብረተሰቡ ባለቤት ሆኖ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ መፍትሄዎቹን የሚያመላክትበት “የምርታማነት ውይይት” በቅርቡ ለመጀመር ዝግጅቱ እንደተጠናቀቀም ነው ክብርት ሚኒስትር ያመላከቱት፡፡ በየደረጃው በቋሚነት በሚካሄው በዚህ “የምርታማነት ውይይት “አጀንዳውን ተወያዮች በራሳቸው የሚለዩና የሚወስኑ ይሆናል፡፡ በውይይቱ ከቤተሰብ ጀምሮ እስከ ማህበረሰብ ድረስ ባሉን ፀጋዎች ልክ ተጠቃሚና ምርታማ ለመሆን የሚገጥሙ ችግሮችንና መፍትሄዎቻቸውን ከማመላከት ባለፈ ተወያዮች የራሳቸውን ድርሻም የሚወስዱበት መድረክ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ የውይይት ሂደቱ ህብረተሰቡ በሙያና ሙያተኛ፤ በሥራና ሠራተኝነት እንዲሁም በታታሪነትና ሠርቶ መለወጥ ላይ አውንታዊ እይታ እንዲኖረው በማድረግ በሥራ ባህላችን ላይ አብዮት መፍጠር የሚያስችል እንደሆነም ነው የተመላከተው፡፡ ከዚህም ባሻገር ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት ከመፍጠር እና ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አኳያም ውይይቱ የራሱ የሆነ አበርክቶ የሚኖረው ሲሆን ዴሞክራሲያዊ የውይይት ባህልን በማሳደግም የሚጫወተው ሚና የላቀ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡ የምርታማነት ውይይቱ ባለቤት በየደረጃው ያለው ህብረተሰብ እንደሆነና ለስኬታማነቱ ለዚሁ ዓላማ ተብለው የሚመረጡ አመቻቾች ሚናቸው የማይተካ እንደሆነም ተመላክቷል፡፡ በየደረጃው የሚገኘው የዘርፉ አመራርና ፈፃሚ ባለሙያ” የምርታማነት ውይይቱ “እና አጠቃላይ የሪፎርም ሥራዎች የታለመላቸውን ግቦች እንዲያሳኩ ቁርጠኛ አመራር እንዲሰጡ እና እሴት አካይ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸው ነው በመድረኩ ላይ የተገለፀው፡፡
en_USEN
Scroll to Top