Mols.gov.et

“የማኅበረሰብ-አቀፍ ውይይት ለሥራ ባህል እድገትና ምርታማነት!”

February 19, 2024
“የማኅበረሰብ-አቀፍ ውይይት ለሥራ ባህል እድገትና ምርታማነት!” የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ምርታማነት ማረጋገጥ የሚያስችል የማህበረሰብ አቀፍ ውይይት ለማስጀመር በአመቻችነት የሚሳተፉ የአሰልጣኞች ሥልጠና ሁለተኛ ዙር መድረክ በሲዳማ እና በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ መካሄድ ጀምሯል። የጅግጅጋውን መድረክ በንግግር ያስጀመሩት የሱማሌ ክልል ብልጸግና ጽ/ቤት ኃላፊ ኢንጅነር መሀመድ ሻሌ እንደገለጹት፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የጀመረው በሥራ ባህል ላይ የሚደረገው ማህበረሰብ አቀፍ ውይይት ለዘመናት ተሸክመነው የቆየውን ድህነትና ኋላቀርነት ማራገፍ የሚስችል አዲስ መንገድ ነው ብለዋል። የሀዋሳውን መድረክ በንግግር የከፈቱት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ኃላፊ እና የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ገቢሳ በበኩላቸው፣ የማህበረሰብ አቀፍ የምርታማነት ውይይት በትኩረት መተግበር ከተቻለ የሥራ ባህል በመቀየር በኩል ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል። መድረኩ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ከኦሮሚያ፣ ከድሬዳዋ ከሀረሪ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ከደቡብ ኢትዮጽያ እና ከሱማሌ ክልሎች የተወጣጡ አንድ ሺህ የሚጠጉ ሰልጣኞች እየተሳተፉበት ይገኛል።
en_USEN
Scroll to Top