Mols.gov.et

የሙኒክ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር ለመስራት መዘጋጀቱን አስታወቀ።

June 23 , 2023 

በክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የተመራ ልዑካን ቡድን ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያለውን አጋርነት እና ትብብር ለማጠናከር እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም ያለመ የሥራ ጉብኝት በጀርመን እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚህም የልዑካን ቡድኑ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት ከሙኒክ ቴክኒክኒካል ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር መስራት የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ ይህን ተከትሎም የሙኒክ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ከኢፌዴሪ የቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑ አስታውቋል። ዩኒቨርሲቲው እንዳስታወቀው ከኢንስቲትዩቱ ጋር የሚጀምረው የትብብርና ቅንጅት ሥራ ውጤታማ እንዲሆን የምሁራን ስብስብ (ቲንክ ታንክ ግሩፕ) ይቋቋማል፡፡ የሚቋቋመው የምሁራን ስብስብም የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ቀጣይነት ላለው ልማት ያለውን አበርክቶ የሚያልቁ የጥናትና ምርምር እንዲሁም የፈጠራ ሥራዎችን የሚሰራ ይሆናል፡፡ ይህም በሙኒክ ዩኒቨርሲቲ እና በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት መካከል የተጀመረውን አጋርነትና ትብብር በትምህርትና ሥልጠና እንዲሁም በቴክኖሎጂና ጥናትና ምርምር እንዲዳብር መንገድ የሚከፍት ነው፡፡
en_USEN
Scroll to Top