Mols.gov.et

የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና ከስደት ተመላሽ ዜጎችን ለማቋቋም የተዘጋጀ መመሪያ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

October 21, 2023
የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና ከስደት ተመላሽ ዜጎችን ለማቋቋም የተዘጋጀ መመሪያ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን እንደገለፁት ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን የመከላከልና ከስደት ተመላሾችን መልሶ የማቋቋም ሀላፊነት አለብን። ለዜጎች ከፍተኛ የሥራ ዕድል እየፈጠርን ያለነው በሀገር ውስጥ ሥራዎች ላይ ነው። ከዚህ አልፎም ዜጎችን በህጋዊ መንገድ ወደውጭ ሀገር ለሥራ እናሰማራለን፡፡ ለዚህም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ብቻ ሳይሆን ከሌሎች በጉዳዩ ላይ ከሚሰሩ ተባባሪ አካላት ጋር በመሆን አካላዊና አዕምሯዊ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሀገር የሚመለሱ ዜጎችን ችግር ፈትቶ በዘላቂነት ወደሥራ ለማሰማራት እየተሠራ ነው ብለዋል ። በመድረኩ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና ከስደት ተመላሽ ዜጎችን ለማቋቋም የተዘጋጀ መመሪያ ቀርቦ ውይይት እየተካሄደበት ይገኛል፡፡
Scroll to Top