Mols.gov.et

“የመደበኛ ፍልሰት ትሩፋቶች ለወጣቶች የሥራ ዕድል፣ ለክህሎት ልማት እና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ”

February 26, 2024
“የመደበኛ ፍልሰት ትሩፋቶች ለወጣቶች የሥራ ዕድል፣ ለክህሎት ልማት እና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው 5ኛው የምስራቅ አፍሪካ የሚኒስትሮች የፍልሰት ጉዳዮች ፎረም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመምከር እንደቀጠለ ነው፡፡ ዛሬ በነበረው ውይይት በክህሎት ልማት እና በወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረቱን አድርጓል፡፡ በዚህም ከአባል ሀገራቱን፣ ከዓለም አቀፉ የፍልሰተት ድርጅትና ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስትታት /ኢጋድ/ የባለሙያዎች ቡድን በቀጠናው በክህሎት ልማትና በወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራው መስክ የተገኙ ስኬቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት አካሂዷል፡፡
en_USEN
Scroll to Top