Mols.gov.et

የመንግስት ተቋማት ለዜጎች የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች…

March 6, 2024
የመንግስት ተቋማት ለዜጎች የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ውጤታማ ለማድረግ በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተዘጋጀውን የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ በሙከራ ደረጃ ለማስተግበር የሚያስችል ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በመካሄድ ላይ ይገኛል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ፖሊሲው በፓይለት ደረጃ ከሚተገበርባቸው ሚኒስቴር መ/ቤቶች መካከል አንዱ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል፡፡ በመድረኩ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌን ጨምሮ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል::
en_USEN
Scroll to Top