Mols.gov.et

የመንግስትና የግል ዘርፉን አጋርነት …

December 15, 2023
የመንግስትና የግል ዘርፉን አጋርነት ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ተጠቆመ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ለማስፈን በሚያደርገው ጥረት የመንግስትንና የግሉን ዘርፍ አጋርነት ለማላቅ እየሰራ ነው። በዚህም የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከሳልማ ፈርኒቸር ባለቤት እና ሥራ አስኪያጅ አቶ አምላክቸር ስዩም ጋር በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ ወጣቶችን በተለያዩ የእንጨት ሥራ ሙያዎች ማሰልጠን፣ ማብቃት፣ ወደ ሥራ እዲገቡ ማድረግ፣ የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው ማድረግ እና በዘርፉ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን አቅም ለመገንባት ላይ ከመግባባት ላይ ተደርሷል። በመድረኩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተለያዩ ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር ስትራቴጂያዊ አጋርነትን ማሳደግ በሪፎርሙ ትኩረት ከተሰጣቸው ተግባራት መካከል አንዱ መሆኑና በተለይ የመንግስትና የግል ዘርፉን አጋርነት ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ተጠቁሟል።
en_USEN
Scroll to Top