የመልካም ልብና ሥራ ጥምረት …
የብዙ ተሰጥኦዎችና ሙያዎች ባለቤትና ሥራ ፈጣሪ ከሆነችው ውድ እህቴ የትናየት ታምራት እና ባልደረቦቿ ጋር በጋራ መስራት ስለምንችልባቸው ጉዳዮች ላይ ተስፋ ሰጭ ምክክር አድርገናል::
በውይይታችን በክህሎት ልማትም ሆነ በሥራ እድል ፈጠራ ዙሪያ በርካታ በትብብር ልንሰራባቸው የምንችል ጉዳዮች እንዳሉ ተረድተናል::
በሀገር ፍቅር ስሜት ለውጥ ለማምጣት ለምታደርጉት ጥረት እና ቁርጠኝነት ልባዊ አድናቆቴ እና በተለይም በእናቶችና ህጻናት ዙሪያ እያበረከታችሁ ላለው ማህበራዊ አገልግሎት ጥልቅ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ::
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!