Mols.gov.et

የላቀ ስኬት ለዜጎች ተጠቃሚነት…

January 7, 2024
የላቀ ስኬት ለዜጎች ተጠቃሚነት…. የሥራና ክህሎት ሚንስቴር የዜጎችን ድህንነትና ጥቅም በማስጠብቅ ህጋዊ የውጭ ሃገር የሰራተኛ ስምሪት በዘመናዊ መንገድ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል። ህጋዊ የውጭ ሃገር የሰራተኛ ስምሪት ለዜጎች የተሻለ አማራጭ እንዲሆን የሚያስችሉ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ሰፊ የሪፎርም ስራዎች እየተከናወኑ የሚገኙ ሲሆን ዜጎች ያለምንም እንግልት እንዲሁም ከፓስፖርት እና ከጤና ምርመራ ክፍያዎች ውጪ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ወደ ውጭ ሄደው ደህንነታቸው፣ መብታቸው እና ጥቅማቸው ተከብሮ መስራት የሚችሉበት ፈጣን አገልግሎት የሚያገኙበት በቴክኖሎጂ የታገዘ የአሰራር ስርዓት ተዘርግቷል። በመሆኑም በዘርፉ በማኑዋል አሰራር ይሰጥ ከነበረው አገልግሎት በወር ከ5.6 እጥፍ በላይ የዘረፉን አፈጻጸም ማሰደግ ተችሏል። ባለፈው በጀት ዓመት የነበረውን 127,000 ወደ ውጭ ሃገር የማሰማራት ከፍተኛ አፈጻጸም በያዘነው በጀት ዓመት ከ 144,000 በላይ ዜጎችን በ5 ወራት በማሰማራት በዘርፉ ሃገራችን ያላትን የሰራተኛ ስምሪት ታሪካዊ ቁጥር ከፍተኛውን ቁጥር ማሳካት ተችሏል። በዚህም በመካከለኛው ምስራቅ ከ14 ሃገራት በላይ ዜጎችን ለሥራ ከሚልኩ ሃገራት በ2ተኛ ደረጃ ላይ እንድንገኝ አድርጎናል፡፡ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተፈጠረ ጠንካራ ቅንጅት፣ በሚንስቴር መስሪያቤቱ በተዘረጋው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና የአሰራር ስርዓት እንዲሁም በሚደረግ ክትትልና ድጋፍ በውጭ ሃገር የሰራተኛ ስምሪት በየወሩ እያደገ የሚገኝ አፈጻጸም እየተመዘገበ ይገኛል።
en_USEN
Scroll to Top