Mols.gov.et

የሊቢያ የሥራና መልሶ ማቋቋም ሚኒስትር …

April 25, 2024
የሊቢያ የሥራና መልሶ ማቋቋም ሚኒስትር ክቡር ሚስተር አሊ አቡአዙም ጋር በጋራ መስራት በምንችልባቸው ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አካሂደናል፡፡ ረጅም ዓመታትን ባስቆጠረው የኢትዮጵያና የሊቢያ ግንኙነት በአጠቃላይ ትብብር መስክ በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ የተለያዩ የስምምነት ሰነዶች መፈረማቸውን መነሻ በማድረግ በሥራ ሥምሪት መስክ በጋራ ለመስራት በሚያስችሉን ነባራዊ ሁኔታዎች ላይም ተወያይተናል፡፡ በዚሁ መነሻነት ኢትዮጵያ በከፊል የሰለጠነ እና የሰለጠነ የሰው ኃይል ለሊቢያ የሥራ ገበያ ለማቅረብ በሚያስችላት ሁኔታዎች ላይ መክረናል፡፡ በሊቢያ ሥራ ገበያ ላይ ካለው የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎት ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በጋራ ለማከናወን እንዲሁም ሊቢያን መልሶ በመገንባት ሂደት በሰለጠነና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሀይል ስምሪት ላይ የበኩላችንን ሚና ለመወጣት ውይይት አካሂደን ከስምምነት ላይ ደርሰናል፡፡ በተለያየ መንገድ ዜጎች ለህገወጥ አዘዋዋሪዎች ተጋላጭ መሆናቸ ይታወቃል:: ይህ የጀመርነው ስምምነት ይህንን ተጋላጭነት የሚቀንስ በሂደትም የሚያስቀር ይሆናል ተብሎ ይታመናል::
en_USEN
Scroll to Top