Mols.gov.et

ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ የበለጸገችና ጠንካራ ሀገርን ለመገንባት ቴክኖሎጂ ማልማት፣ መጠቀምና ለስታርታፖች ምቹ ሁኔታ መፍጠር ወሳኝ ነው፡፡ ክቡር አቶ ደመቀ መኮንነ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር

October 24, 2023
ለመጀመሪያ ጊዜ በፈጠራና ቴክኖሎጂ ላይ የሚሰማሩ አካላት ተቋማዊ ቅንጅት ፈጥረው ለአዳዲስ ሥራ ፈጠራና ጀማሪ ቢዝነሶች ምቹ ሥነ-ምህዳር ለመፍጠር በጋራ የሚሰሩበት (The Next Ethiopian StartUp Initiative -NEST) መርሃ ግብር ዛሬ ተጀምሯል፡፡ መርሃ ግሩን በይፋ ያስጀመሩት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን እንደገለጹት፣ የበለፀገ ማህበረሰብ ለመገንባት ጊዜውን የዋጀ ቴክኖሎጂ ማልማትና መጠቀም ወሳኝ ነው፡፡ ስለሆነም ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ የበለጸገችና ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ቴክኖሎጂ ማልማት፣ መጠቀምና ለስታርታፖች ምቹ ሁኔታ መፍጠር ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የጀመሩት ይህ አዲስ መርሃ ግብር ኢትዮጵያን ጠንካራና ተወዳዳሪ የሚያደርግ መሆኑን የጠቆሙት ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን መርሃ ግብሩ ለስታርትአፖች፣ ኢንተርፕሩነሮች እና የፈጠራ ባለሙያዎች ምቹ ስነ-ምህዳር መፍጠር የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው፣ በኢትዮጵያ አይቻልምን አሸንፈው መውጣት የቻሉ ጥቂት ስታርትአፖች አሉ፡፡ እነዚህን ስታርትአፖች ለማብዛትና ለማሳደግ መንግስት ባለፉት አምስት ዓመታት ተግዳሮቶቻቸውን ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በቅርቡም ስነ-ምህዳሩን ለማስፋት እና በህግ ማዕቀፎች ለማስደገፍ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
Scroll to Top