Mols.gov.et

ዕምቅ አቅሞችን በራስ አቅም …

January 21, 2024
ዕምቅ አቅሞችን በራስ አቅም … የጎለበተ ህዝባዊ የሥራ ፈጠራ ባህል መዳበር የስራ ተነሳሽነትን ከማሳደጉም ባለፈ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት፣ ዘላቂ ልማትና ሰላም ለማምጣት ትልቅ አሻራ ይኖረዋል:: ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን በያዘው የክልል አቅም ግንባታ ፕሮግራም አካል በሆነው ጥምረት በተጠሪ ተቋሙ የኢንተርፕሩነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት በኩል ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ አመራር በአዲስ እሳቤ ህዝብ-መር የሥራ ባህል ንቅናቄን በመፍጠር የክልሉን ፀጋ አልምቶ የሀገር ኢኮኖሚን ለመደገፍ ያለመ የፐብሊክ ሴክተር ኢተርፕሩነርሺፕ ፕሮግራም አስጀምረናል:: ስልጠናው የሥራ ፈጣሪነት አስተሳሰብን ለማስረጽ እና የፈጠራ ባህልን ለማሳደግ ውጤታማ የጎንዮሽ ትስስር እንዲሁም የአመራር እና ህዝብ አሻግሮ የጋራ ግብን የማየትና ቅንጅት የመፍጠር አስፈላጊነትን በአንክሮ ያስገነዘበ ነው:: የኢንተርፕሩነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ተ/ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሀሰን ሁሴን እና ባልደረቦቻቸው ይህንን አይን ገላጭና የራስ ዕምቅ አቅምን ተጠቅሞ ሀብት የማፍራት፤ ከራስ አልፎ የሀገር ምሰሶ መሆን የመቻል መንገድን የሚያመላክት፤ የሥራ ፈጠራ ክህሎትን የሚያዳብር እና የሚያነሳሳ ስልጠና ለክልሉ አመራር እንዲደርስ በማድረጋቸው ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው:: የቤንሻንጉል ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አሻድሌ ሀሰን ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው ካቢኔያቸውን አስተባብረው በስልጠናው ተሳታፊ በመሆናቸው እንዲሁም የክህሎት ልማትና ሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ በአትኩሮት ለመስራት ለሰጡት አመራርና ላሳዩት ቁርጠኝነት ላቅ ያለ አድናቆቴና ምስጋናዬ ይድረሳቸው::
en_USEN
Scroll to Top