Mols.gov.et

ዓለም አቀፍ ዕድሎችን ለመጠቀም…

December 22, 2023
ዓለም አቀፍ ዕድሎችን ለመጠቀም… በዲጂታል ኢንዱስትሪ አውትሶርሲንግ ሥራዎች ኢትዮጵውያን ወጣቶችን ተጠቃሚ በሚሆኑባቸው ጉዳዮች ላይ ከሚሰራው የሌማት ኘሮጀክት መስራቾች ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገናል፡፡ በውይይታችን በዲጂታል ኢንዱስትሪ የአውትሶርሲንግ ሥራ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጥር እና የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ በመሆኑ መንግስትም ለዘርፉ ልማት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ፤ የ2025 የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ መዘጋጀት፣ የአይ.ሲ.ቲ. ፓርክና የቴሌኮም መሠረተ ልማትን ለማስፋፋት እየተደረገ ያለው ጥረት ለዚህ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን ተመልክተናል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (E-LMIS) በሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ለምቶ ወደ ሥራ መግባቱም በአውትሶረሲንግ ቢዝነስ ለሚሰማሩ ሁሉ ምቹ መደላድል እንደሚፈጥር አይተናል። በዘርፉ ሀገራችንን ተጠቃሚ እንድትሆን የሚደረገው ጥረት ሀገራችን ያላትን ሰፊ የወጣት ቁጥር ከግምት ያስገባና ኢትዮጵያን በልዩነት ሊያስተዋውቅ በሚያስችል መልኩ የተቃኘ መሆን እንደሚገባውም ተግባብተናል፡፡ በዲጂታል ኢንዱስትሪ አውትሶርስ ተደርገው ከሚከናወኑ ሥራዎች ኢትዮጵውያን ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ለሚንቀሳቀሱት የሌማት ኘሮጀክት መስራቾች ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ!
en_USEN
Scroll to Top