Mols.gov.et

ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚሰማራው የሰው ኃይል እያደገ መምጣቱ ተገለጸ

October 10, 2025
ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚሰማራው የሰው ኃይል እያደገ መምጣቱ ተገለጸ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ፣ በከሳዑዲ አረቢያ የሙሳነድ ፖርትፎሊዮ ዋና ስራ አስፈፃሚ ካሊድ አልቱኪ ከተመራ ልዑክ ጋር በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዙሪያ በሰራው የማሻሻያ ሥራዎችን ተከትሎ ወደ ሳውዲ የሚሰማራው የሰው ኃይል እያደገ መጥቷል፡፡ የዜጎች መብት፣ ደህንትና ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አኳያም ሁለቱ ሀገራት ተቀራርበው እየሰሩ ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በሂደቱ የሚሰተዋሉ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም የሰለጠነና በከፊል የሰለጠነ የሰው ኃይል ወደ ሳውዲ ለማሰማራት በሥራ ላይ ያለውን የውጭ አገር የሥራ ስምሪት አዋጅ በማሻሻል ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል፡፡ በታካሞል ሆልዲንግ የሙሳነድ ፖርትፎሊዮ ዋና ስራ አስፈፃሚ ካሊድ አልቱኪ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ቀዳሚ የሰው ኃይል አቅራቢ አገር መሆኗን ገልፀዋል፡፡ በቀጣይም ወደ ሳውዲ ዓረቢያ የሚሰማራውን የሰው ኃይል ቁጥር ለማሳደግም ፍላጎት እንዳላቸው አብራርተዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top