Mols.gov.et

“ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራውን በማዘመን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማሻሻል ይገባል።” ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

August 31, 2023
ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራን በማዘመን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማሻሻል እንደሚገባ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ፡፡ ክብርት ሚኒስትር ይህን የገለፁት በሀረሪ ክልል በተካሄደው የብልፅግና ፓርቲ የአቅም ግንባታ ዘርፍ የ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት መድረክ ላይ ነው፡፡ እሴት አካይ ኢንተርፕራይዞች ላይ በማተኮር ውጤታማ የቢዝነስ ልማት ስርአትን በመቅረፅና በመዘርጋት ከዘርፉ የሚገኘውን ጠቀሜታ ማጎልበት እንደሚገባን ነው ክብርት ሚኒስትር የገለፁት። እሴት ሰንሰለትን መሰረት ባደረገ የሥራ ዕድል ፈጠራ የቤተሰብ ንግድን ማጠናከር፣ የሥራ ባህልን በማሻሻል እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም ምርትና ምርታማነት ማሳደግ ላይም በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top