ከጣሊያን የልማት ትብብር ዋና ዳይሬክተር ሚ/ር ስቴፋኖ ጋቲ ጋር የሁለቱ ሀገራት በተለያዩ መስኮች የልማት ትብብር እና የቀጠናው ፍልሰት አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ጠቃሚ ውይይት አካሂደናል::
ጣሊያን በቀጣይ G7 የምትመራ መሆኑን ተከትሎ ለአፍሪካ በተለይም ለኢትዮጵያ በሰጠችው ትኩረት ቀደም ሲል እየተደረጉ ካሉ ድጋፎች ባሻገር በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በክህሎት ልማትና አቅም ግንባታ ረገድ በትብብር ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰናል::
ለነበረን ፍሬያማ ውይይት ሚ/ር ስቴፋኖ ጋቲን እና ባልደረቦቻቸውን ከልብ አመሰግናለሁ!