Mols.gov.et

ከዓለም ባንክ ዳይሬክተር በኢትዮጵያ ሚ/ር ኦስማን ዲዮን ጋር…

December 6, 2023
ከዓለም ባንክ ዳይሬክተር በኢትዮጵያ ሚ/ር ኦስማን ዲዮን ጋር በክህሎት በቅተው ፍሬ ያፈሩ የብሩህ አእምሮና ወርቃማ እጆች ባለቤት ወጣቶቻችንን ጎብኝተናል፣ አበረታተናል:: ከሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ተውጣጥተው፤ በየደረጃው የተካሄዱ የፈጠራ ውድድሮችን አልፈው ለተጨማሪ ስልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ በኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በልዩ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሀሳቦች ማበልፀጊያ መርሃ ግብር ያካተትናቸው የፈጠራ ውጤት ባለቤት ወጣቶች የተሰሩ ቴክኖሎጂዎችን ጎብኝተናል፡፡ ከወንድሜ ሚ/ር ኦስማን ዲዮን ጋርም እነዚህን ወጣቶች እና የቴክኖሎጂ ውጤቶቻቸውን ወደ ሰፊ ምርት ቀይረን ገበያ ወጥተው ኢኮኖሚያችንን ለመደገፍና በርካታ የስራ እድል ለመፍጠር እንዲያስችሉን በጋራ መስራት በምንችልባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት አድርገናል፡፡ የዓለም ባንክ የቀጠናው ዳይሬክተር ሚስተር ኦስማን ዲዮን ካለዎት የተጣበበ ጊዜ ወስደው የወጣቶቻችንን ብርቅዬ የአእምሮ ውጤቶች ለማየትና ብርታት ለመሆን ለሰጡት ትኩረት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረስዎ፡፡
Scroll to Top