Mols.gov.et

ከውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት ኤጀንሲዎች ማህበራት የቦርድ አባላት ጋር…

April 26, 2024
ከውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት ኤጀንሲዎች ማህበራት የቦርድ አባላት ጋር ዜጎችን በውጭ ሀገር የሥራ ገበያ ላይ ደህንነታቸውና ክብራቸው ተጠብቆ በውጤታማነት ለማሰማራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጏል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ሥርዓትንና ህግን እንዲሁም የዜጎችን ክብር በጠበቀ መልኩ ተግባራዊ እንዲሆን የሚያስችል የሪፎርም ሥራዎችን ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ ዜጎችንም ሆነ ሀገርን ከዘርፉ ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር ጉልህ ሚና እንደሚኖረው በውይይቱ በጉልህ ተነስቷል፡፡ ዜጎችን ለእንግልትና ለአደጋ የሚዳርጉ ህገወጥ ድርጊቶችን ከመግታት አንፃር መንግስትና በውጭ አገር ሥራ ሥምሪት ላይ የተሰማሩ ኤጀንሲዎች በጥምረት መስራት እንደሚኖርባቸውም አፅንዖት ተሰጥቶት ተነስቷል፡፡ ከተለያዩ መዳረሻ ሀገራት የሚቀርበውን የሰለጠነና በከፊል የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎት ለማሟላት በሚያስችል መልኩ ኤጀንሲዎች ራሳቸውን ማጠናከርና አቅማቸውን ማሳደግ እንደሚኖርባቸውም ከመግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
Scroll to Top