Mols.gov.et

ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያ ቀዳሚው ትኩረት የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ሊሆን እንደሚገባ ተጠቆመ

December 4, 2024
ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያ ቀዳሚው ትኩረት የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ሊሆን እንደሚገባ ተጠቆመ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አሰራሮችና አተገባበር ዙሪያ ከሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤቶች እና ሥራ አስኪያጆች ጋር ውይይት ተደርጓል። በውይይቱ ከ800 በላይ ተሳታፊዎች የተካፈሉ ሲሆን በዘርፉ የአሰራር ስርዓት፣ በአፈጻጸም ላይ በሚታዩ ችግሮች፣ በመደበኛ ቁጥጥር እና አቤቱታ አቀራረብና አፈታት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በዝርዝር ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡ ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያ ቀዳሚው ትኩረት የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ በመድረኩ ኤጀንሲዎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የአሰራር ስርዓት ተጠቅመው አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡ ይህንን የማይከተሉ ኤጀንሲዎች ላይ መንግስት አስፈላጊ የሆነ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድም ተመላክቷል፡፡
en_USEN
Scroll to Top