Mols.gov.et

ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ- መስተዳድር…

April 1, 2024
ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ- መስተዳድር ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በዘርፋችን ርብርብና ልዩ ትኩረት በሚጠይቁ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አካሂደናል፡፡ ውይይታችን ከዚህ ቀደም በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነትን ከማስፈን አኳያ የተግባባንባቸውን ጉዳዮች ይበልጥ ለማላቅና የተቀመጡ ሀገራዊ ግቦቻችንን በማሳካት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለመ ነው፡፡ በዚህም ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተያዘውን ግብ ለማሳካት በቅንጅት የመስራት ጅማሯችንን ማስፋት እንደሚገባን ተግባብተናል፡፡ ከውይይቱ ባለፈ በኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ተኪ ምርቶች ላይ ሀገራዊ አቅም ለመፍጠር የተጀመሩ ሥራዎችን በጋራ ያየን ሲሆን ይህም ከቴክኖሎጂ አኳያ እንደ ሀገር ተስፋ ሰጪና የሁሉንም ድጋፍና ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት-ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና በሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ላይ መስራት ከሀገራዊ ግቦች ስኬት በላይ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ጉዳይ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቅንጅት አብሮ ለመስራት ላሳዩን ቁርጠኝነት እና እየሰጡ ላሉት ቁርጠኛ አመራር ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳቸው፡፡ የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
en_USEN
Scroll to Top