Mols.gov.et

ከአፋር ክልል ም/ል ርዕሰ መስተዳድርና የሥራና ክህሎት ቢሮ

November 16, 2023
ከአፋር ክልል ም/ል ርዕሰ መስተዳድርና የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ኤሌማ አቡበከር ጋር በዘርፉ ልማትና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል። በውይይታችን የክልሉን እምቅ የመልማት አቅም በአግብቡ አልምቶ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በክህሎት ልማትና በአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት ዘርፉ ላይ የተከናወኑ ሥራዎችና የዘርፉን ማነቆዎች መፍታት የሚቻልባቸው አቅጣጫዎችን ተመልክተናል። የአፋር ክልል ም/ል ርዕሰ መስተዳድርና የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ኤሌማ አቡበከር ወደ ዘርፉ በመጡ በአጭር ጊዜ ክልላዊ አቅምን አስተባብሮ በመስኩ የሚታዩ ዕድሎችን ለመግለጥና ማነቆዎችን ለመፍታት እያደረጉ ላለው ጥረት ከልብ የመነጨ አክብሮትና ምስጋናዬ ይድረስዎ።
en_USEN
Scroll to Top