Mols.gov.et

እየተከናወነ የሚገኘው የድጋፍና ክትትል ሥራ የሪፎርሙ ሥራዎች …

December 20, 2023
እየተከናወነ የሚገኘው የድጋፍና ክትትል ሥራ የሪፎርሙ ሥራዎች እና አበይት ተግባራት በተጨባጭ መሬት ወርደው እየተተገበሩ ስለመሆኑ ማየት የሚያስችል እንደሆነ ተጠቆመ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ባለፉት አምስት ወራት የተከናወኑ ሥራዎች ላይ ያተኮረ ሀገር አቀፍ የድጋፍና ክትትል እያረገ ይገኛል፡፡ የድጋፍና ክትትል ቡድኑን አስመልክቶ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ መሃመድ እንደገለጹት፣ ሚኒስቴሩ በዘርፉ አዳዲስ እሳቤዎች ዙሪያ ለዘርፉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት ወደ ሥራ መገባቱን አስታውሰው አሁን ላይ የድጋፍና ክትትል ቡድን በተለያዩ አካባቢዎች ተሰማርቷል፡፡ ይህ የድጋፍና ክትትል ቡድኑ የሪፎርም ሥራዎች እና ሌሎች አበይት ተግባራት መሬት ወርደው እየተተገበሩ ስለመሆኑ እና ክፍተቶችን ለይቶ መሙላት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡ በአፈጻጸም ሂደት የሚታዩ ጉድለቶች ከመለየትና እርማት ከመስጥ ባለፈ የተሻለ አፈጻጸም የታየባቸው ክልሎችን ተሞክሮ በመቀመር ወደ ሌሎች ለማስፋት ድጋፍና ክትትሉ ፋይዳው የላቀ መሆኑንም ነው ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ ያነሱት፡፡ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሰልጣኞች ቅበላ የንቅናቄ ሥራ፣ የተቋማቱን የመልማት አቅማቸውን ባገናዘብ መልኩ እየተከናወነ የሚገኘውን የዞኒንግ እና ዲፈረንሼሽን ትግበራ፣ በአንድ ማዕከላት እየተከናወነ የሚገኘውን የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ምዝገባ ሁኔታ፣ የቤተሰብ ንግድ እና የመንግስታዊ ድጋፎች አፈጻጸም፣ ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት በመፍጠር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሁም የሙያ ብቃት ምዘና ሥራዎች በድጋፍና ክትትሉ በልዩ ትኩረት የሚታዩ ጉዳዮች ናቸው፡፡
en_USEN
Scroll to Top