Mols.gov.et

እሴት ሰንሰለትን የተከተለ የሥራ ዕድል ፈጠራ

August 31, 2023
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተለያዩ ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አስተባባሪዎች እና የገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ ዳይሬክተሮች ባዘጋጀው መድረክ እሴት ሰንሰለትን የተከተለ የሥራ ዕድል ፈጠራ አስመልክቶ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ ሥልጠናውን የሰጡት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የግብርና ሙያ ደረጃ እና ብቃት ምዘና ዴስክ ኃላፊ ዶ/ር ፍቃዱ አለማየሁ፤ ከጥሬ እቃ አቅርቦት ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ የምርት ሂደቶች ላይ እሴት የሚጨምር አካሄድ መከተል፤ ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ በላይ ዘላቂ እና አድማሱ የሰፋ የሥራ እድል መፍጠር ያስችላል ብለዋል፡፡
Scroll to Top