ኤክስፖው የጀመርነውን የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነት ለማሻሻል ልምድ ያገኘንበት ነው፡፡
ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ
የቴክኒክና ሙያ ሚኒስትር ዴኤታ
ስድስተኛው የሳውዲ አረቢያ የሰው ሃብት ኤክስፖ በሪያድ እየተካሄደ ነው፡፡
በሪያድ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን እና ኤግዚቢሽን ማዕከል እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ኤክስፖ የሀገሪቱ ታላላቅ የሰው ሀይል ቅጥር ኩባንያዎችን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ፣ እስያ እና የአፍሪካ ሀገራት እየተሳተፉ ይገኛል፡፡
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የሚመራ የልዑካን ቡድንም በኤክስፖ በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡
ከኤክስፖው ጎን ለጎን የልዑካን ቡድኑ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የልምድ ልውውጥ ያደረገ ሲሆን በሪያድና ጂዳ ከሚገኙ አምባሳደሮች እና ቆንጽላዎችና የአጄንሲ ማህበራት በተገኙበት በዘርፉ በሚስተዋሉ ችገሮች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄዷል
በዚህም ኤክስፖው ሀገራችን ከቤት ውስጥ ሥራ ባለፈ ሰፊ የሆነ የሰለጠነና በከፊል የስለጠነ የሰው ኃይል ያላት መሆኑን ለማስተዋወቅ እድል የሰጠና የጀመርነውን የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነትን ለማሻሻል ልምድ የተገኘበት መሆኑን ክቡር ዶ/ር ተሻለ ተናግረዋል፡፡