Mols.gov.et

ኢንተርፕራይዞች የሚያመርቷቸው ምርቶች ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን እንዲተኩ፣ በአገር ውስጥ ገበያ ተፈላጊ እንዲሁም በዋጋና ጥራት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ መስራት እንደሚገባቸው ተጠቆመ

August 30, 2023
ይህ የተገለፀው ለስድስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ኢንተርፕራይዞችን የማንቃት ስልጠና ሲጠናቀቅ ነው፡፡ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢንተርፕሪነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት እና ከተባበሩት ድርጅት የልማት ፕሮግራም እንዲሁም ከኮሪያ የልማት ኤጀንሲ( ኮይካ) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የኢንተርፕራይዞችን የማንቃት የስድስት ተከታታይ ቀናት ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ፣ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን እንደገለጹት፣ የምርምር ተቋማት የኢንተርፕራይዞችን ችግሮች የሚፈቱ ጥናትና ምርምሮችን እንዲያካሄዱና አዳዲስ ሃቦችን እንዲያመነጩ፤ የፋይናንስ ተቋማት ለኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ አቅርቦትን እንዲያመቻቹ እና በኢንተርፕርነርሽፕ ሥነ ምህዳር ውስጥ ወሳኝ የሆኑ አካላት በንቃት እንዲሳተፉ መንግስት የድርሻውን እየተወጣ ነው፡፡ መንግስት በዚህ መልኩ የሚያደርገው ጥረት ውጤታማ የኢንተርፕሪነርሺፕ ሥነ- ምህዳርን ዕውን ለማድረግ ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡ ኢንተርፕራይዞች የሚያመርቷቸው ምርቶች ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን እንዲተኩ በአገር ውስጥ በህበረተሰቡ እንዲወደዱና እንዲፈለጉ እንዲሁም በዋጋም በጥራትም ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በትጋትና በትኩረት መስራት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top