Mols.gov.et

“ኢንተርፕራይዝ ምስረታ ጥራት ያለው ሥልጠና እና ሥራን የሚያገናኙ ተቋማት ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡ “ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

August 31, 2023
ኢንተርፕራይዝ ምስረታ ጥራት ያለው ሥልጠና እና ሥራን የሚያገናኙ ተቋማት ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡ ክብርት ሚኒስትር ይህን የገለጹት ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ የሆኑ የግብርና ኮሌጆች የትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎች ዙሪያ ያተኮረው የውይይት መድረክ ማጠቃለያ ላይ ነው፡፡ በማጠቃለያ መድረኩ ላይ ክብርት ሚኒስትር በሰጡት የሥራ መመሪ እንደገለጹት፣ በዘርፉ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የእሳቤ ለውጥ ፈጣንና ተለዋዋጭ የሆነውን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ያስገባ ነው፡፡ በዚህም ያለፈውን ጊዜ የሚያካክስ፣ የአሁኑን ፍላጎት የሚመልስ እና የቀጣዩን ከግምት ውስጥ የሚያስገባ ጠንካራ ሥራ መስራትን ይጠይቃል፡፡ የታሰበውን ለውጥ ለማምጣትም በፍጥነት፣ በብዛት እና በጥራት ማምረት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም ተቋማቱ ከጠባቂነት የተላቀቁ፣ ፈጠራን የተላበሱ እና ኢንተርፕሪነሪያል መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ አንፃር በተቋማት የሚካሄደው የኢንተርፕራይዝ ምስረታ ጥራት ያለው ሥልጠና የሚሰጡ እና ሥራን የሚያገናኙ ተቋማት ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል፡፡ ዘመናዊና የተቀናጀ የግብርና ልማት ሥራ የሚሰሩ ኢንተርፕራይዞች ማደራጀት ተቋማቱን የልህቀት ማዕከላት ከማድረግ በሻገር በተቋማቱ ማህበረሰብ ለሚነሱ ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ በራሳቸው አቅም ምላሽ መስጠት እንዲችሉና በሂደት ተወዳዳሪ ተቋማት የመገንባት ዓላማም እንዳለው ነው የጠቆሙት፡፡ ተዝቆ የማያልቅ ሀብት ይዘን በምርጫና በውሳኔ ደሀ መሆን አይኖርብንም ያሉት ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ይልቁንም በምርጫና በውሳኔያችን ኢኖቬቲቭ የሆነ ተቋም መገንባት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top