ኢንስቲትዩቱ የዞኑን የቱሪስት ካርታ፣ የጉዞ ጥቅል እና የባህላዊ ምግብ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለስልጤ ዞን አስተዳደር አስረከበ።
ኢንስቲትዩቱ ሰነዱን ያስረከበው በወራቤ ከተማ ‹‹ ቱሪዝም ለአረንጓዴ ልማት፣ አረንጓዴ ልማት ለቱሪዝም›› በሚል መሪ ሀሳብ በተከበረው የቱሪዝም ቀን ማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ ነው፡፡
ሰነዱን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አሊ ከድር ነው ያስረከቡት፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ወራቤ ዞን ከባህል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ በመተበባበር ያዘጋጃቸው ሰነዶች የዞኑን የቱሪስት ካርታ፣ የጉዞ ጥቅል እና 18 አይነት የባህላዊ ምግብ ዝርዝርና አሰራርን የያዙ ናቸው፡፡
በእለቱ ከሰነድ ርክክቡ ባለፈ በጥናት የተለዩት እና የአሰራር ሰነድ የተዘጋጀላቸው 18ቱ የባህላዊ ምግቦች የቀረቡ ሲሆን የተመረጡ የቱሪስት መስብ ቦታዎችም ተጎብኝተዋል፡፡