Mols.gov.et

ኢንስቲትዩቱ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ያለውን የገበያ ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እየሰራ እንደሆነ ተጠቆመ

December 14, 2024
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያ ያለውን የገበያ ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ኢኒስቲትዩቱ ለሥራ ገበያ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠትና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማስፋት የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡ በሥልጠናው የመክፈቻ መርሃ ግብር ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት፤ የሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ተጠቃሚ የሚሆኑ ዜጎች ተወዳዳሪና የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ የሚያስችል ነው። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የዜጎችን መብት ደህንነትና ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ እንዲሆን አቅጣጫ አስቀምጦ ተግባራዊ እየተደረገ ሲሆን በዚህ መሰረትም ኢኒስቲትዩቱ እስካሁን ለበርካታ ዜጎች ተግባር ተኮር ሥልጠናዎችን መስጠት ችሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዘርፉ ላለው የሥራ ገበያ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠትና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማስፋት የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡ በስልጠናው ከተለያዩ ክልሎች የተወጣጡ የፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኞች እንደተካፈሉም ገልፀዋል፡፡ በዚህ በጀት አመት 150 ሰልጣኞች በሦስት ዙሮች የሰለጠኑ ሲሆን የተሰጠው ሥልጠና በምግብና መጠጥ መስተንግዶ፣ በቤት አያያዝ እና በምግብ ዝግጅት ላይ ያተኮረ ተግባር ተኮር መሆኑንና ኢንስቲትዩቱ የሚሰጠውን ስልጠና በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል የተቋሙ አመራሮች ጠቁመዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ የሥልጠና እና የተቋማት አቅም ግንባታ ዴስክ ሀላፊ አቶ ተመስገን በቀለ በሦስተኛው ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ስልጠናውን ያገኙ አሰልጣኞች ወደ ተቋማቸው ሲመለሱ እንደሀገር የተሰጣቸውን ኃለፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top