Mols.gov.et

ኢትዮጵያ የሚገባት ስፍራ ላይ እንድትገኝ…

April 7, 2024
ኢትዮጵያ የሚገባት ስፍራ ላይ እንድትገኝ… ሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ የልማት ፀጋዎች ያሏት ሀገር ነች፡፡ እነኚህን ፀጋዎች በአጋባቡ አልምተን መጠቀም ብንችል በአጭር ጊዜ ከድህነትና ኋላ ቀርነት መላቀቅ ይቻላል፡፡ ለዚህም ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሞካከርናቸው ሥራዎች ያገኘናቸው ውጤቶች ህያው ማሳያ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት የማድረጉ ውጥንም ከዚህ እሳቤ የሚመነጭ ነው፡፡ ይህን ትልቅ ግብ ከዳር ለማድረስ የብዙ ተዋንያንን ያላሰለሰ ጥረት የሚጠይቅ ቢሆንም በሚታሰበው የኢኮኖ እድገት ውስጥ የስታርት አፖች ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ይፋ የተደረገው “ስታርት አፕ ኢትዮጵያ” እንደ ሀገር ያለንን የመልማት ፀጋ ብቻ ሳይሆን ተግዳሮቶቻችንም ጭምር ወደ መልካም አጋጣሚነት የሚቀይሩ፣ ከሀገር ውስጥ አልፎ በቀጣናውና በዓለም አቀፍ ደረጃም ችግሮችን መፍታት የሚችሉና ፈጠራ የታከለባቸው የሥራ ሀሳቦች ያላቸውን ዜጎች መደገፍ የሚያስችል ነው፡፡ ይህ ስርዓት ወጣቶች የራሳቸውን ሀገር እንድትመቻቸው አድርገው መስራት የሚችሉበት አውድ ከመሆኑም ባሻገር ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ የሚገባትን ቦታ እንድታገኝ የሚያስችል፡፡ በመሆኑ በሂደቱ ሚና ያላቸው ተዋንያን መደላድሉን ለመፍጠር በቅንጅት መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ስታርት አፕ ውድድር አዘጋጅ ሆና የተመረጠች ሲሆን ፈጠራ የታከለበት የሥራ ሃሳብና ምርት ያላችሁ ዜጎች ይህን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም (https://www.giig.africa/) መመዝገብና በውድድሩ ላይ ተካፋይ መሆን እንደምትችሉ እንገልፃለን፡፡ ከጥንስሱ እስከ ውጤቱ ቁርጠኛ አመራር ለሰጡን ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር አክብሮቴና ምስጋናዬ የላቀ ነው፡፡ የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
en_USEN
Scroll to Top