Mols.gov.et

“ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰላምና መረጋጋትን እንዱሁም ሥራ ፈጣሪ ዜጎችን የምትፈልግበት ወቅት ላይ ትገኛለች።”

February 8, 2024
“ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰላምና መረጋጋትን እንዱሁም ሥራ ፈጣሪ ዜጎችን የምትፈልግበት ወቅት ላይ ትገኛለች።” ክቡር አቶ አወል አርባ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከክልል እና ተጠሪ ተቋማቱ ጋር የሚያካሂደው የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም የግምገማ እና የምክክር መድረክ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መካሄድ ጀምሯል። በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አወል አርባ እንደገለፁት፤ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰላምና መረጋጋትን እንዱሁም ሥራ ፈጣሪ ዜጎችን የምትፈልግበት ወቅት ላይ ትገኛለች። ድህነት፣ ሥራ አጥነትና ህገ ወጥ ስደት የህዝባችን መሠረታዊ ከሚባሉት ችግሮች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ይህንን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ የጋራ ርብርብን ይጠይቃል። “ሥራ በክህሎት ይመራ!” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው ይህ መድረክ ይህንና መሰል ችግሮችን በመፍታት ሰላምና መረጋጋት እንዲሠፍንና የታቀደው ልማትና ብልፅግና እውን እንዲሆን ፋይዳው የላቀ ነው ብለዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሰምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን በበኩላቸው፤ መድረኩ ሰኬቶቻችንና የጋጠሙ ተግዳሮቶች የምንፈትሽበት እና ለቁልፍ ችግሮቻችን ቁልፍ የሆኑ መፍትሄዎች የሚቀመጡበት ነው ብለዋል።
en_USEN
Scroll to Top