Mols.gov.et

ኢትዮጵያ በብሪክስ የሥራ ስምሪት የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

September 10, 2024
ኢትዮጵያ በብሪክስ የሥራ ስምሪት የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡ ጉባኤው የወቅቱ የብሪክስ ሊቀመንበር በሆነችው በሩሲያ እየተካሄደ ይገኛል ። በመድረኩ ከአባል ሀገራቱ የተውጣጡ ልዑካን በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጥራ፣ የሥራ ላይ ደህንነትና ጤንነት እንዲሁም የሥራ ዕድል ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ምክክር እያደረጉ ይገኛል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ ልዑካን እየተሳተፉ ይገኛሉ። የሥራና ክህሎት ሚንስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ በመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ በበይነ መረብ መልዕት ያስተላለፉ ሲሆን በሠራተኞች ደህንነት እና በኢንዱስትሪ ግንኙነት ዙሪያ የኢትዮጵያን ተሞክሮንም አጋርተዋል።
en_USEN
Scroll to Top