Mols.gov.et

ኢትዮጲያውያን የማዕዱ ተቋዳሽ ሆነዋል !!

October 27, 2023
የ2023 የዓለም-አቀፉ የጀማሪ ቢዝነስ (ስታርትአፕ) ሽልማት የአፍሪካ ጉባኤ በመዲናችን አዲስ አበባ ተካሂዶ በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል! ለአፍሪካ ስታርትአፖች ምቹ የሆነ ስነ-ምህዳር መፍጠር እና ስኬታማ የሆኑ የአፍሪካ ስታርትአፖች፣ ሥራ ፈጣሪዎች እንዲሁም የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ተገቢውን የክህሎት፣ የእውቀት፣ የቴክኖሎጂና የገንዘብ ድገፍ የሚያገኙበትን ሁኔታ መፍጠር ዓላማውን ባደረገው በዚህ መድረክ ከመላው አፍሪካ ከተመረጡ 70 ስታርታፖች መካከል 15 የመጨረሻ አሸናፊዎች እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ የ2022/23 የግሎባል ኢኖቬሽን ኢኒሼቲቭ ግሩፕ (GIIG) የአፍሪካ አሸናፊ ተብለው የተለዩትና እውቅና የተሰጣቸው ስታርትአፖች የአካባቢያቸውን ብቻ ሳይሆን በየተወዳደሩበት መስክ በመላው ዓለም ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ባላቸው አቅም ነው፡፡ ከአሸናፊዎቹ መካከል በአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ቡና ላይ የተሰማራው ‹‹Coffee Resurrect ›› የተሰኘ የኢትዮጵያ ስታርትአኘ አሸናፊ ሆኖ እውቅና ተሰጥቶታል፡፡ መድረኩ የታለመለትን ግብ ያሳካ እና በዘርፉ ሰፊ የመልማት ዕድሎች ያላን እንደሆነ በተጨባጭ ያረጋገጠልን ሆኖ አልፏል፡፡ ለመርሃ ግብሩ ስኬት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ አመራርና ባለሙያዎች እንዲሁም የብዙሃን መገናኛ ተቋማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ ስለሆነም ለዚህ ትልቅ መድረክ አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ ሁሉ ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነው፡፡
en_USEN
Scroll to Top