አጋርነት ለውጤት…
ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) የኢትዮጵያ ተወካይ ሳሙኤል ባይድ ዶው ጋር በቅንጅት መስራት በምንችልባቸው ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አካሂደናል፡፡
በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
በውይይቱ ላይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከክህሎት ልማት፣ ከሥራ ዕድል ፈጠራ እና ከአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ አኳያ ተቀርጸው እየተተገበሩ የሚገኙ የሪፎርም ሥራዎችን በዝርዝር እንደተመለከቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተናግረዋል፡፡
አቶ ሳሙኤል ባይድ ዶው በበኩላቸው እየተከናወኑ የሚገኙ የሪፎርም ሥራዎች መሰታዊ ለውጥ የሚያመጡና ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ጭምር ተሞክሮ የሚሆኑ በመሆኑ ሥራዎቹን ማስፋት እንደሚገባ እና የሪፎርም አጀንዳዎቹን ጨምሮ በጋራ በሚለዩ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተጨባጭ ሥራ ለመስራት ድርጅቱ ዝግጁ እንደሆነ አረጋግጠውልናል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም(UNDP) የኢትዮጵያ ተወካይ ሳሙኤል ባይድ ዶው በትኩረት ጉዳዮቻችን ላይ ተጨማሪ አቅም ለመሆንና በጋራ አብሮ ለመሥራት ላሳዩን ቁርጠኝነት እናመሰግናለን በልዋል ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል ፡፡