Mols.gov.et

አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦችን በመተግበር…

December 12, 2023
አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦችን በመተግበር ህዝብን በፍፁም ቅንነት፣ ታማኝነትና እውነተኛነት የማገልገል ባህል ያላቸው መንግስታዊ ተቋማትን ዕውን ማድረግ የፕሮግራሙ ዋንኛ ዓላማ ነው! ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ፈጠራን የተላበሰ አሠራርንና ችግሮችን የመፍታት ባህልን በተቋማት የመገንባት ዓላማ ያለው Public Sector Innovation Lab የሚል ስያሜ ያለው ፕሮግራም በቅርቡ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ የዚሁ ፕሮግራም አካል የሆነውና የተቋሙ ካውንስል አባላት በየወሩ ተገናኝተው ተቋማዊና አገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መፍትሔ አፍላቂ ውይይቶችን የሚያደርጉበት Innovation for Development Breakfast Meeting (I4DB) በሚኒስቴር መ/ቤቱ በይፋ ተጀምሯል፡፡ ውይይቱ በየወሩ ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት እስከ 3:00 ሰዓት የሚካሄድ ሲሆን በመድረኩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማት ካውንስል አባላት ይሳተፉበታል። የውይይት መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ባስተላለፉት መልዕክት ባልተቋረጠ መልኩ አዳዲስ ሃሳቦችን ለማመንጨትና ችግሮችን የመፍታት አቅምን ለማሳደግ Public Sector Innovation Lab ፕሮግራም በሚኒስቴር መ/ቤቱና ተጠሪ ተቋም በሆነው በኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢኒስቲትዩት ትብብር ተግባራዊ መደረጉን ገልፀዋል፡፡ መሰል ፕሮግራሞች ፈታኝና ተለዋዋጭ የሆኑትን የዓለማችንን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል ኢኖቬቲቭ ሃሳቦችን ለማመንጨት ዕድል የሚሰጡ መሆናቸውንም ክብርት ሚኒስትር አስረድተዋል፡፡ ፕሮግራሙን ተግባራዊ ለማድረግ ከአንድ ዓመት ለበለጠ ጊዜ ቅድመ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን በመጥቀስም አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦችን በመተግበር ህዝብን በፍፁም ቅንነት፣ ታማኝነትና እውነተኛነት የማገልገል ባህል ያላቸው መንግስታዊ ተቋማትን ዕውን ማድረግ የፕሮግራሙ ዋንኛ ዓላማ መሆኑንም ክብርት ሚኒስትሯ አስረድተዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top