Mols.gov.et

አዳዲስ ዕድሎች… ሲዊዲን ሀገር ከሚገኝ ”ሚልዮማንኒግ“ ከተባለ ኩባኒያ ጋር አብሮ መስራት የሚያስችለንን የመግባቢያ ስምምነት ዛሬ ተፈራርመናል፡፡

August 29, 2023
ከሀገራዊ ለውጡ ጋር የተሰናሰለ ተቋማዊ ሪፎርም እያደረግንበት ከሚገኙ ዘርፎች መካከል የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ፍልሰት አይቀሬ ነባራዊ ሁኔታ መሆኑን ከግምት በማስገባት ከሀገር ውስጥ ባለፈ የዓለምን የሥራ ገበያ ለመጠቀምና ፍልሰትን በአግባቡ ለማስተዳደር በትኩረት እየሰራን እንገኛለን፡፡ በዚህም ፍላጎቱ ያላቸው ዜጎች ብቻ በቂ እውቀትና ክህሎት ይዘው እንዲሁም መብትና ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ተለያዩ የዓለም ሀገራት ህጋዊ በሆነ መንገድ ተሰማርተውና ሰርተው ተጠቃሚ የሚሆኑበት በቴክኖሎጂ የታገዘ የአሰራር ስርዓት ተዘርግቷል፡፡ ዛሬ ያደረግነው ስምምነትም ፍላጎቱ ያላቸው ዜጎች ህጋዊ በሆነ የአሰራር ስርዓት ሲዊዲንን ጨምሮ ወደ ተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚያደርጉትን ጉዞ ከማሳለጥና አዳዲስ ክህሎት እንዲያገኙ ከማድረግ ባለፈ በክህሎት የዳበረ የሰለጠነ የሰው ሃይል ለሀገር ውስጥ የሥራ ገበያ በማዘጋጀት ረገድም የራሱ ሚና ይጫወታል፡፡ ለሥራው መሳካት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሲዊዲን የኢትዮጵያ ኤምባሲን፣ ለሥራው ተግባራዊነት ላሳዩን ቁርጠኝነትና ላደረጉት ጥረት የሚልዮንማንኒግ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሊ ካሊልን እንዲሁም ሥራው ወደ ተግባር እንዲቀየር ላደረጉ የሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ፡፡
en_USEN
Scroll to Top