አዲስ የትብብር ምዕራፍ …
በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በፈጠራና ቴክኖሎጂ ላይ የሚሰማሩ መንግስታዊ ተቋማት፣ የግል ዘርፉ እና የፈጠራ ባለሙያዎች ጠንካራ ተቋማዊ ቅንጅት በመፍጠር ለአዳዲስ ሥራ ፈጠራና ጀማሪ ቢዝነሶች ምቹ ሥነ-ምህዳር መፍጠር ላይ የሚያጠነጥን መርሃ ግብር ጥቅምት 13 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ እናስጀምራለን፡፡
ይህ መርሃ ግብር ሀገር አቀፍ የጀማሪ ቢዝነሶች ኢንሼቲቭ (The Next Ethiopian StartUp Initiative -NEST) የሚሰኝ ሲሆን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኢንተርፕሩነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ ያዘጋጀውና በዘርፉ የተለያዩ ባለድርሻና አጋር አካላትን ወደ አንድ በማምጣት ጠንካራ ተቋማዊ ጥምረት መፍጠርን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
መድረኩ ጀማሪ ቢዝነሶች ከክህሎት ልማት፣ ቴክኖሎጂ፣ ሥራ ዕድል ፈጠራና የወጣቶች ተሳትፎ ጋር በማጣመር እንደ ሀገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማምጣት አስቻይ መደላድልን ለመፍጠር ሁነኛ ሚና ይኖረዋል፡፡
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!