Mols.gov.et

አማካሪ ቦርዱ አካታችነትን በተግባር …

December 30, 2023
”አማካሪ ቦርዱ አካታችነትን በተግባር ያስመሰከረና አካል ጉዳተኝነት የተሻለ መሪ ከመሆን እንደማያግድ በተግባር ያሳየ ነው::“ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ለማስተር ካርድ ፋውንዴሽን የወጣቶች አማካሪ ቦርድ አባላት ልምዳቸውን አካፈሉ፡፡ ክብርት ሚኒስትር ከወጣት አመካሪ ቦርዱ አባላት ጋር በነበራቸው ቆይታ በክህሎት ልማትና ሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የተነሱላቸውን ጥያቄዎች ያብራሩ ሲሆን የሕይወት ተሞክሮሯቸውንም አካፍለዋቸዋል፡፡ የወጣት አማካሪ ቦርዱ አባላት አካታችነትን በተግባር ያስመሰከረና አካል ጉዳተኛነት የተሻለ መሪ ከመሆን እንደማያግድ ያሳየ ነው ያሉት ክብርት ሚኒስትር ወጣቶቹ በትውልዶች መካከል እውቀትን የማመጋገብን ጠቀሜታ ተረድተው ከልምዶቻችን ለመማር ያነሷቸው ጥያቄዎች ብልህነታቸውና ብስለታቸውንም ጭምር የሚያሳይ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
Scroll to Top