Mols.gov.et

“ትኩረታችን ምርትን ብቻ ሣይሆን ምርታማነትን ማሳደግ ነው።”

June 18, 2024
“ትኩረታችን ምርትን ብቻ ሣይሆን ምርታማነትን ማሳደግ ነው።” ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች በሀገራዊ የዘርፎች አፈፃፀም እና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አካሄዱ። በመድረኩ የማክሮ ኢኮኖሚው ሀገራዊ የዘርፎች አፈፃፀምና የተገኙ ውጤቶች እንዲሁም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ11 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2017 በጀት ዓመት አቅጣጫዎች ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት፣ መድረኩ ሁሉም አመራርና ሠራተኛ በማክሮ ኢኮኖሚው ሀገራዊ የዘርፎች አፈፃፀምና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ተገቢውን ግንዛቤ ይዞ የድርሻውን መወጣት እንዲችል ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው፡፡ አፈፃፀሙ በአስተቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ሆነን መስራትና ውጤታ ማምጣት እንደምንችል ያሳየ ነው፡፡ ይህም በቀጣይ ትጋትና ብርታት መለያችን ሆኖ ከቀጠለ የታሰበውን ሀገራዊ ልማትና ብልጽግናን እውን ማድረግ እንደምንችል የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር የተደረገው ጥረትም ተስፋ ሰጪ እንደሆነም ነው ክብርት ሚኒስትር ያመላከቱት፡፡ እንደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና በኢንዱስትሪ ሰላም ዙሪያ የምንሰራተው ሥራ እንደ ሀገር የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት የሚያስችሉ እንደሆነ ያመላከቱት ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ትኩረታችን ምርትን ብቻ ሣይሆን ምርታማነትን ማሳደግና የተሟላ ኢኮኖሚያዊ ነፃነትን ማግኘት ነው። ለዚህም ሁሉም የበኩሉን ለመወጣት ርብርብ ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top