Mols.gov.et

ትምህርት ቤቱ እያንዳንዱ ተማሪ በመክሊቱ ስልጠና ማግኘት የሚችልበት ማዕከል ይሆናል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

January 10, 2025
ትምህርት ቤቱ እያንዳንዱ ተማሪ በመክሊቱ ስልጠና ማግኘት የሚችልበት ማዕከል ይሆናል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል የሚሆን ‹‹የ21ኛው ክፍለዘመን ማህበረሰብ አቀፍ ትምህርት ቤት›› ግንባታ አስጀመረ፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ኢንስቲትዩቱ የሚያስገነባውን የ21ኛው ክፍለ-ዘመን ማህበረሰብ አቀፍ ትምህርት ቤት ግንባታ በይፋ አስጀምረዋል፡፡ በማስጀመሪያ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ፣ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች እና የኢንስቲትዩቱ አሰልጣኞች ተገኝተዋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ግንባታውን ሲያስጀምሩ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፤ ትምህርት ቤቱ እያንዳንዱ ተማሪ በመክሊቱ ስልጠና ማግኘት የሚችልበት ማዕከል ይሆናል ብለዋል፡፡ በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፓሊሲ ላይ የተቀመጠውን የትምርት ስርዓቱን ቮኬሽናላይዝ የማድረግ ግብ ለማሳካት ከሚሰሩ ስራዎች አንዱ መሠል ተቋማትን መገንባት ይገኝበታል ብለዋል፡፡ የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር በበኩላቸው የ21ኛው ክፍለ-ዘመን ማህበረሰብ አቀፍ ትምህርት ቤት የክህሎት ማሳደጊያ ቦታ እንዲሆን ታስቦ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ የመጀመሪያ ዙር ግንባታ የህጻናት መጫወቻን ጨምሮ በ1 ሺ 6 መቶ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚሰራ ሲሆን ከሁለት ወራት በኋላ ተጠናቆ ለስራ ዝግጁ እንደሚሆን ግንባታውን የጀመረው የግንባታ ተቋራጭ ገልጿል::
en_USEN
Scroll to Top